መድሕን ወይም ዋስትና

መድሕን በሚገቡበት ጊዜ የጤና መረጃ እንዲያቀርቡ የሚጠይቁ አንዳንድ የመድሕን ዓይነቶች አሉ ፡፡ ከነዚህም መካከል የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድሕኖ ናቸው ፡፡

scheduleOppdatert: 22.07.2021

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ከጤና ጋር የተዛመደ መድሕን ሲገቡ የጤና ሁኔታን መግለጫ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ ፡፡ ይህ የሚያቀርቡት የጤና መረጃ ኩባንያው የግለሰቡን የጤና ሁኔታ ግምገማ የሚመስርትበት በመሆኑ ነው፡፡ መረጃው ለመድሕንዎ ትክክለኛ ዋጋ እና የውሎች መስፈርትን ለመወሰን ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ ለኢንሹራንስ ወይም መድሕን የሚያመለክት ማንኛውም ግለሰብ እንደዚህ ያለ የጤና መረጃ የመስጠት ግዴታ  አለበት ፡፡ መረጃው ትክክል ካልሆነ ግን መድሕን የተገባበት ሁኔታ ከተከሰተ ካሳ የመድሕን ኩባንኛው አይከፍልም​​፡፡ የጤና መረጃዎች ምን ግዜም በጥብቅ ጥንቃቄ  ይያዛሉ ፡፡

በኤች አይ ቪ ሕሙማን እንድዚሁ የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድሕን እንደማንኛውም ግለሰብ  መድሕን መግባት ይችላሉ ፡፡ አደጋው በግለሰቡ የግል ሁኔታዊ ግምቶች ላይ በመሠረት ይሰላል። ይህ ማለት ደግሞ ከከባድ የጤና ችግሮች ጋር የሚታገሉ ሰዎች መድሕን ለምግባት ከፍ ያል ችግር ሊጋጥማቸው ይችላል ማለት ነው ፡፡ ነገር ግን  ስኬታማ ህክምና በፍጥነት የወሰዱ ግለሰቦች ግን በመደበኛ የሆነ መድህን ወይም  ኢንሹራንስ እንደ ማንኛውም ግለሰብ መግባት ይችላሉ ወይም ደግሞ ከፍ ያለ የመድህን ክፍያ በመክፈል መግባት ይችሉ ይሆን ይሆናል።

ሌሎች ዋስትናዎች ወይም መድህኖች

ኤች አይ ቪ ለሌሎች ኢንሹራንሶች ሊያመጥ የሚችለው ችግሮችን በሚመለከት ሁኔትው እንዲገለጽ የሚጠየቀው ዋስትናው በጤና ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ላላቸው ኢንሹራንሶች ወይም ዋስትናዎች ብቻ ነው። ለእንደዚህ አይነት ዋስትናዎች የጤና የምስክር ወረቀቶችን መጠየቅ  ይፈቀዳል፡፡ ይኸውም ለየሞት አደጋ መድሕን ፣ የአካል ጉዳት አደጋ መድሕን ፣ የሕክምና መድሕን ፣ የጤና መድህን ፣ በሕመም መቅረት የሚጋለግል መድሕን እና የአደገኛ የሕመም አደጋ መድህን ናቸው ፡፡

 የይዘቶች መድሕን እና የጉዞ መድን በሚገቡበት  ጊዜ የጤና መግለጫን ማግኘት ጠቃሚ አይሆንም ፡፡ አብዛኛዎቹ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንዲሁ ለአደጋ መድሕን የጤና መግለጫን አይጠይቁም ፡፡ የአደጋ መድሕን የግል ሕይወት መድሕን ነው ስለሆነም የሕይወት አደጋ መድሕን አይደለም ስለዚሕ  የጤና የምስክር ወረቀት መጠየቅ ከሚችሉበት ዋስትናዎች ጋር በተመሳሳይነት በአንድ  ቡድን ውስጥ ይገኛል ፡፡ ሆኖም የጤና መረጃ ለእንዲህ ዓይነቱ መድሕን ጠቃሚ አይሆንም ፣ ስለሆነም ከአደጋ መድሕን ጋር በተያያዘ የጤና መረጃን  መጠየቅ አይፈቀድም ፡፡

የጉዞ መድህን

ወደ የጉዞ ዋስትና እና ስለ ኤች አይ ቪ መድሕን በሚመጣበት ጊዜ አግባብ ያለው ጠንቅ ያለ አስተሳሰብን መያዙ ጠቃሚ ነው ፡፡ በደንብ የሕክምና ክትትል የሚሰጠው የኤችአይቪ ኢንፌክሽን ሕመምተኛ ከሆኑና እና በኖርዌይ ውስጥ የሕክምና ክትትልን የሚያገኙ  ከሆነ እና በጉዞው ወቅቶች የተረጋጋ ሁኔት ላይ ከአሉ  በኤች አይ ቪ በሽታ ድንገተኛ ወይም ያልተጠበቀ ለውጥ ከተከሰተ የመድሕን ክፍያን ወጭዎችን መሸፍንን ያገኛሉ ፡፡

የጉዞ መድህን የማይሸፍነው በኤች አይ ቪ ጋር በተዛመደ ምክንያቶች በተደጋጋሚ ሆስፒታል በመግባት የጤና እርዳታ የሚወስዱ ከሆነና እንደዚሁም ከመጎዞ በቅርብ ጊዜ በፊት የሚወሰዱት የመድኃኒት ላይ ለውጥ ከአደረጉ ነው። ይኽም ሕክምናዊ ወይም አገልግሎታዊ ነገሮች ላይ የተመሰረትም ሁኒታም ቢሆንም ነው ።

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።