camera_altFoto: Crestock
ምርመራው ውጤቱ አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆነ
ለኤች አይ ቪ ምርመራው ውጤት አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆን ወደ ተላላፊ በሽታ የጤና ተቋም ተልከው ይሕክምና እግልግሎት እንዲያገኙ እድል ይቀርብሎታል ፡፡ ከኖርዌይ ውስጥ ከኤች አይ ቪ በሽታ ጋር ለተያዙ ህክምናዎች በሙሉ በነፃ ይሰጣሉ ፡፡
ኤች አይ ቪ በአሁኑ ዘመን ሥር የሰደደ ዘላቂ የሆነ የህመም ሁኔታ ሲሆን እንደማንኛውም ሰው ግን ረጅም ዕድሜ ዘመን መኖር ይቻላል ፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ረጅም እድሜ ለመብቃት የኤችአይቪ ሕክምናውን ወዲያውኑ መጀመር እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህ ለራሱ ጥቅም ብቻ ሳይሆን በአንጻራዊ ሁኔታው ሲታይ ከአጭር የህክምና እርዳታ በሁላ ግለስቡ በሽታውን ወደ ሌላ ግለሰብ ከማስተላለፍም ነጻ ይሆናል ማለትም ጭምር ነው። የሕክምና ክትትሉ የሚከናወነው በተላላፊ በሽታ ክፍል በሆስፒታል ውስጥ ነው ፡፡ ሕክምናው አንዴ ከተጀመረና እንደሚሠራ ወይም ስኬታም ውጤን መስጠቱን ከተረጋገጠ በኋላ በዓመት ለአንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የጥንቃቄ ምርመራውን ማድረግ በቻ በቂ ይሆናል ፡፡ የኤች አይ ቪ ሕክምና ዛሬ በጣም ጥቂት የተጎዳኝ ጉዳቶች ሲኖሩት አብዛኝውም ጊዜም በቀን አንድ ክኒን ብቻ ነው መውሰድም የሚያስፈልገው ።
Les også
schedule14.01.2023
→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?
ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።
schedule31.12.2021
→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።
በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።